የድረ ገፅ ስያሜ:- ፀ ጋ ዬ
1. ዓላማ
2. ተግባር
3. መረሐ ግብር
4. መምሪያዎች
5. ስያሜ
6. ዓርማ
1. ዓላማ፣
በጠቅላይ ሚኒስትር
ሄሮድስ መለስ ዜናዊ የሚመራው
ጎሳዊና ፋሽስታዊ አገዛዝን
ግባተ መሬት
ለማፋጠን በሚካሄደው
ዲሞክራሲያዊ ትግል፣
- የግንዛቤን
አድማስ በማስፋፋት የህሊናን
መሰናዶ ለማሟላት፣
- የሕዝቡን ዲሞክራሲያዊ
ትግል በሀሳብ ለማገዝ፣
- እንዲሁም ሁለገብ
የሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮችን
በብዕር ለዛ ለመቃኘት
ይሆናል።
በተጨማሪም
የ 21ኛውን ምዕተ ዓመት ተረካቢ
የሆኑ ልጆችን በሚመለከት
በጣም በጥቂቱ የመክፈቻ
መሠረት ለመጣል ( የቻለ
አስፍቶ ሊቀጥል ይችላል፣
ማሳው ድንግል ነውና )፣
2. ተግባር፣
2.1 የድርሻችንን
ለመወጣት ድልድይ መዘርጋት
/ መንገድ ለመክፈት /
2.2 የልምድ፣ የዕውቀት
እና የተመክሮ ምክለት
ለመፍጠር፣
2.3 የስደትን ሕይወት
ለማናገር፣
2.4 የሰው ልጅ የነቃው
የህሊና ክፍል በእህልና
በመጠጥ ብቻ አይኖርም::
የሰው ልጅ
የነቃው የህሊና
ክፍል ትልቅ
ውስብስብ ረቂቅ ምጥቅ
ልዩ ማሳ ነው:: ማሳው ደግሞ በመስኖ
መልማት አለበት::
መስኖው
ደግሞ ጥበብ ነው:: ጥበብ
ደግሞ ረቂቅ የሆነ ቅዱስ
ፀጋዊ መንፈስ ነው:: ስለዚህ እኛ እና
የጥበብ
መንፈስን ጥበብን ወይንም
ጥበብና እኛን በሰማንያ
እንደአቅማችን ለማጋባት
ነው::
3. መረሐ ግብር፣
እንደሚታወቀው
መርሀ ግብር መሪ የተግባር
ትልም ማለት ነው::
ለአንድ ድርጅት
ወይንም ለግል ሕይወትም
መርሀ ግብር ያስፈልገዋል::
መርሀ ግብር የሌለው አካል
ዓይን የለውም:: ዓይን ካልኖረምደግሞ የፈለገ ዓይነት
ብቃት ቢኖረው አይደለም
ሌላውን እራሱን እንኳን
መምራት አይችልም::
መርሀ ግብር የተግባር ትልም፣ መሪ፣አቅጣጫ አመልካች መንገድቀያሽ መሀንዲስ ነው:: ስለሆነም ድህረ ገጻችን ሦስት ደረጃ ( ምዕራፍ)ያላቸው ትልሞች አሉት።
3.1 የአጭር ጊዜ
_ ከአንድ ሳምንት እስከ
አንድ ወር፣
3.2 የመካከለኛ
ጊዜ _ ከአንድ ወር አስከ
አንድ ዓመት፣
3.3 የረዥም ጊዜ
_ ከአንድ ዓመት እስከ አምስት
ዓመት፣
አሁን በአለን
አቅምና ሁኔታ በአጭር
ጊዜ መርሀ ግብራችን መንቀሳቀስ
አንጀምራለን:: ማለትም
በእጃችን ባሉ ነገሮች
ዙሪያ መርሐ ግብራችን
አኃዱ ይላል:: ቢያንስ ለእያንዳንዱ
መምሪያ በወር አንድ ጽሑፍ
ማውጣት የሚያስችል ሙሉ
መሰናዶው ተጠናቋል::
4. መምሪያዎች፣
ቃና
ማዕዶት
አብረታት
የሎሬት ተስፋ
ዕድምታ
5. ስያሜ፣-
ፀጋዬ ድህረ
ገፅ፣
6. ዓርማ፣-
በአለም ካርታ
ውስጥ የአፍሪካ ካርታ፣
በአፍሪካ ካርታ ውስጥ
የኢትዮጵያ
ካርታ፣- በኢትዮጵያ
ካርታ ውስጥ የብላቴን
ጌታ ሎሬት ፀጋ ገ/መድኅን
ፎቶ፣
6.1 የዓርማ ትርጉም፣
. የዓለም ካርታ
መዐቀፉ የሆነበት ምክንያት
ጥበብ ድንበር፣ ወሰን
የማይገድበው በመሆኑ፣
. ድህረ ገፃችን
ዓለም አቀፋዊ ስለሆነ፣
. የሌሎች ሀገር ፅሑፎች፣ ግጥሞች ልናስተናግድ ሀሳቡ ስላለን ነው::


